ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኒውካስል ተጋጣሚዎቻቸውን ሲረቱ ቶትንሃም ተሸነፈ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 01/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኒውካስል ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ በቶትንሃም በኢፕስዊች ታውን ተረቷል።
በሜዳው ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የማንቸስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ብሩኖ ፈርናንዴዝ፣ ቪክቶር ክርስቲያንሰን እና አሌሃንድሮ ጋርናቾ ከመረብ አሳርፈዋል።
በሲቲ ግራውንድ ኖቲንግሃም ፎረስትን የገጠመው ኒውካስል 3ለ1 አሸንፏል።
አሌክሳንደር አይሳክ፣ ጆይሊንተን እና ሃርቬ ባርንስ የኒውካስልን የድል ግቦች ከመረብ ሲያሳርፉ ሙሪሎ ለኖቲንግሃም ፎረስት የማስተዛዘኛዋን ግብ አስቆጥሯል።
ቶትንሃም በበኩሉ አዲስ አዳጊውን ኢፕስዊች ታውንን በሜዳው አስተናግዶ 2ለ1 ተረቷል።
ፕሪሚዬር ሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ተጠባቂው የለንደን ደርቢ በቼልሲ እና አርሰናል መካከል በስታንፎርድ ብሪጅ ይካሄዳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች