አርሰናል እና ፒኤስጂ ሽንፈት ሲያስተናግዱ ባርሴሎና እና ባየርሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ 4ኛ ዙር የመጨረሻ መርሐግብር አርሰናል እና ፒኤስጂ ሽንፈትን ሳያስተናግዱ ባርሴሎና እና ባየርንሙኒክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ከሜዳው ውጪ ኢንተር ሚላንን የገጠመው አርሰናል 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የኢንተርን የማሸነፊያ ግብ ሀካን ቻልሃኖግሉ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
በሜዳው አትሌቲኮ ማድሪድን ያስተናገደው ፒኤስጂም 2ለ1 ተሸንፏል።
የአትሌቲኮ ማድሪድን የድል ግቦች ናሁኤል ሞሊና እና አንሄል ኮሪያ ከመረብ ሲያሳርፉ ፒኤስጂን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ዋረን ዛዬር ኤሜሪ አስቆጥሯል።
ባርሴሎና በበኩሉ ከሜዳው ውጪ ዳይናሞ ዛግሬቭን 5ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የካታላኑን ክለብ የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሊቫንዶውስኪ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር፥ኢኒጎ ማርቲኔዝ፣ራፊንሃ እና ፈርሚን ሎፔዝ ቀሪ የድል ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ባየርሙኒክም በሜዳው ጃማል ሙሲያላ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ቤኔፊካን ረቷል።
በሌሎች ጨዋታዎች ክለብ ብሩጅ አስቶንቪላን 1ለ0፣ብረስት ስፓርታ ፕራሃን 2ለ1 ሲያሸንፉ ስቱትጋርት በአታላንታ 2ለ0፣ ፌዬኖርድም በሳልዝቡርግ 3ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ታገደ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ጤናማና ንቁ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ