ሀድያ ሆሳዕና ድሬዳዋ ከተማን አሸነፈ
በኢትዮጵያ ፕሪሚዬርሊግ 7ኛ ሳምንት መርሐግብር ሀድያ ሆሳዕና ድሬዳዋ ከተማን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ሀድያ ሆሳዕና ባለሜዳውን በመርታት ወደ አሸናፊነት በተመለሰበት ጨዋታ ሰመረ ሐፍታይ በ48ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ከቤራዎቹ ነጥባቸውን 7 በማድረስ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ በ8 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ከጠጠር ሜዳ እስከ ፕሪሚየር ሊግ
ቼልሲ ማርኮ ፓሌስትራን አስፈረመ
ሞሮኮ እና ብራዚል ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፉ ጀርመን ተሰናበተች