የምክክር ሂደቱ በመከባበር እውነትን ባህል ያደረገ፣ መሰረታዊ የሀገሪቱን ችግሮች የሚገልፅ እና ኢትዮጵያን የሚመጥን መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ ገለፁ።
ለ3 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ አሰባሰብ ሂደትና የተወካዮች መረጣ በስኬት ተጠናቋል።
የአጀንዳ እና የተወካይ መረጣው እውነትን መሰረት ያደረገ እና ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር፣ በህዝብና በመንግስት መካከል እምነት እንዲፈጠር ማድረግ እና ምክክርን ባህል ማድረግን ያየንበት መድረክ ነው ብለዋል።
የሚዲያ ባለሙያዎችም እንደተመለከቱት የምክክር መድረኩ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት እና ለሀገር ሰላም መሰረት የሚጣልበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም በቀጣይ ከአርብ እስከ እሁድ በሚኖሩ ቀናት የተለያዩ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሀይማኖት መሪዎች እና ተፅእኖ ፈጣሪዎች በራሳቸው ልምምድ የሚመክሩበት ብሎም አጀንዳ የሚመረጡበት መድረክ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ባለፉት ቀናት በተደረገው የማህበረሰብ ውይይትም ሆነ በቀጣይ ቀናት በተፅእኖ ፈጣሪዎች የሚደረገው የምክክር መድረክ ዋና አላማው ሀገራዊ አጀንዳ ማቅረብ፣ በጥልቀት የመጣንበትን መንገድ መፈተሽ እና በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን መምረጥ በመሆኑ በጥራት እንደሚካሄድ ነው ኮሚሽነሩ የገለፁት።
ለ3 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳና የተወካይ መረጣ የተሳካ እንደሆነ ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ከቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽንና ከሐመር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ
በሲዳማ ክልል ለተገኘው ሰላም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነበር – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
የአራቱም ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ