በምክክር ሂደቱ በሁሉም ማህበራዊ መሠረቶች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ ነው – በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ ሴቶች
ሴቶች ስለሀገራቸው የመምከር ኃላፊነት እንዳላቸውም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል ::
እንደሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የምክክር መድረክ በመሳተፋችን እድለኝነት ተሰምቶናል ያሉት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሀገራዊ ምክክር መድረክ ተሳታፊ ሴቶች መካከል ከጎፋ እና ጌዴኦ ዞኖች ወ/ሮ መስከረም ሙላት እና አልማዝ ኃይሉ ፣ በየአካባቢው ባሉ ችሮች ዙሪያ መመካከር መጀመራቸውን ተናግረዋል ።
ወ/ሮ በረከት በዛብህ ከኮሬ ዞን፣ ወ/ሮ አታለለች አያኖ ከኮንሶ ዞን እና ወ/ሮ አርት ማያ ከደቡብ ኦሞ ዞን ከተሳተፉ ሴቶች መካከል ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያን ለማሻገር ሴቶችን ያሳተፈ ምክክር እየተደረገ በመሆኑ ደስተኛ ነን ብለው፣ የአጀንዳ ሐሳባችንን በነጻነት እያቀረብን ነው ብለዋል።
በሁሉም ማህበራዊ መሠረቶች የሴቶች ተሳትፎ የጎላ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ በምክክሩ ሂደቱ ለሴቶች ዕድል ተሠጥቷል ነው ያሉት።
የምክክር መድረኩ በጥሩ ደረጃ መጀመሩን ገልጸው፣ ሴቶች በሐገራቸው ችግሮች ዙሪያ ተመካክረው መፍትሔ ለማስቀመጥ በቡድን ባላቸው ውይይት በነቃ ሁኔታ እየመከሩ እንደሆነ አመላክተዋል።
ሴቶች ከራሳቸው ችግር አልፈው ስለሀገር የመምከር ኃላፊነት እንዳላቸው የተናገሩት ተሳታፊዎቹ፣ ሴቶች የለውጡ አንዱ አካል እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ብለዋል።
በየአካባቢው ያሉ ችግሮች በጋራ እየተመከሩ በመሆኑ መፍትሔዎቹንም በማስቀመጥ ፣ ከምክክሩ በኋላ የኢትዮጵያን ከፍታ እንጠብቃለን ነው ያሉት።
በአስር የማህበራዊ መሠረቶች ከ2 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን የያዘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ፣ የውይይትና ለሐገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች መረጣ የማድረጊያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ዘጋቢ ፡ እስራኤል ቅጣው – ከይ/ጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ