ሀዋሳ መስከረም 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የህዝቡን የልማት እድገት እና ባህል ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ምሁራን በምክንያታዊ ሀሳብ በማገዝ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የስልጤ ዞን አስተዳደር ገለፀ፡፡
የስልጤ ዞን አስተዳደር ከወራቤ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምሁራን የምክክር መድረክ “የምሁራን ሚና ለህብረተሰብ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል በወራቤ ከተማ ተካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩ የተገኙት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካ የህዝቡን ልማት፣ እድገትና ባህል ለማሳደግ በሚደረገው ዘርፈ ብዙ ጥረት ምሁራን በምክንያታዊ ሀሳብ በማገዝ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምሁራን የፈጠራ ሀሳቦችን በማምጣት እና በመተግበር ረገድ ከዞን አልፎ በሀገር እድገት ላይ ያላቸው ሚና ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው በዞኑ እየተደረጉ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የወራቤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እንጅነር ቶፊቅ ጀማል እንደገለፁት የሀገርን እድገት ለማረጋገጥ የሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን እና በአንድ የማህበረሰብ ልማት እድገት እንዲሁም ለውጥ የምሁራን ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ምሁራን የምክንያታዊ ሀሳብ ባለቤት ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምሁራን ሀሳብን በአግባቡ በመተግበር ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት መነሻ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የወራቤ ዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ፣በጥናትና ምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋፆኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
በምክክር መድረኩ ተሳተፊ የነበሩ ምሁራን ለህብረተሰቡ ለውጥ በቀጣይ በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩም ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዞን፣ የወረዳ ባለድርሻ አካላትና ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ዘጋቢ: ሳጂዳ ሙዳስር – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚባክነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን ጥምር ደን መጠበቅ፣ ማስፋትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማዘመን የዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ