የኬሌ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ አማካሪ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባዔ አካሄደ

ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የኬሌ ከተማ ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ሀና ኃይሌ ምክር ቤቱን የመልካም አስተዳደር፣ የግልፀኝነትና ተጠያቂነት እሴቶች ማፍለቂያ ተቋም ለማድረግ ሁሉም ድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባዔ አቶ ምናሉ እንዳለ የ2016 በጀት ዓመት የመሥሪያ ቤቶችን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆኑ አብዛኛው የተሻለ ሆኖ ሳለ የመስክ ምልከታ፣የተሽከርካሪ እጥረት የፎቶ ኮፒ ማሽን እጥረትና ሌሎችም በደካማ ጎን ተገምግሟል።

የኬሌ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ዮሐንስ ኃይሉ የከተማው ፈርጅ ለውጥ ለማድረግ የተሠራው ሥራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸው ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ከተሳታፊዎች መካካል የኮሬ ዞን ምክር ቤት አፈጉባዔ ወይዘሮ አካላት በቀለና አቶ ኦላይሴ ኦያደ በኢንተርፕራይዝ፣ በገቢ አሰባሰብና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል በትኩረት እንዲሠሩ አስተያየት ሰጥተዋል።

ከቋሚ ኮሚቴዎች አቶ ፍራንካ ፍላቴና አቶ ቴወድሮስ ጭርጋ በጀት እንደጸደቀ ወደ ተግባር ያለመግባት ችግሮች መኖሩን አይተው አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ነው የተናገሩት።

የ2017 ዓመት የከተማው በጀት ከመንግሥት ግምጃ ቤት 77 ሚሊየን 979 ሺህ 210፣ ከውስጥ ገቢ 70 ሚሊዮን 654 ሺህ 47 ብር ጠቅላላ 148 ሚሊዮን 633 ሺህ 257 ብር መሆኑ ተገልጿል።

ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን