መምሪያው የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ የ2017 ዓ.ም መሪ የልማት እና መልካም አስተዳደር ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የመንግሥት ረዳት ተጠሪ አቶ ምህረቱ ተፈሪ ዞኑ ህገ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ የሚንቀሳቀስበት መሆኑን ገልጸው ይህን ለማስቀረት ባለድርሻዎች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናረዋል፡፡
በንግድ ሥርዓት የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችል መልኩ፣ ችግሮቹን በመለየት በቀጣይ ለማረም መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት ኃላፊ ወ/ሮ ሠላማዊት ያሬድ ህገ ወጥ የጎዳና ንግድና ኮንትሮባንድን ከመከላከል ባለፈ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ አውጥተው የሚሰሩትን የመደገፍ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
ህገ ወጦችን በሙሉ መከላከል ባይቻልም መቀነስ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
ከተገልጋዮች የሚነሱ ቅሬታዎችን በመለየት በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ለመፍታት በማቀድ በህዝብና በመንግሥት መካከል የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የመምሪያውን የ2016 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀምና የ2017 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ሪፖርት ያቀረቡት በመምሪያው የልማት ዕቅድ ቡድን መሪ አቶ ክብሩ ወጋየሁ በ2016 ዓ.ም ላይ የነበረውን ውስንነቶች በመቅረፍ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
ዘጋቢ ፡ እምነት ሽፈራው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የህብረተሰቡን ጤና ለማጎልበት የዘርፉን ተግባራት በተገቢው ለማሳካት ከምንጊዜውም በተሻለ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
የህዝቡን የልማት ፍላጎቶች ለማሟላትና መንግስታዊ አገልግሎቶችን በተገቢው ለመስጠት የውስጥ ገቢ ግብርን አማጦ ለመሰብሰብ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ