የአቢሲኒያ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ በመመደብ የማዕድ ማጋራት ተግባር አከናውኗል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብዱልበር ሰይድ የመስቀል በአል በጉራጌ ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር ከአባቶች ሲወራረስ የመጣውን የመደጋገፍ፣ የመተሳሰብና የመተባበር ባህል በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልፀዋል።
በዛሬው እለትም ይህን መነሻ በማድረግ የአቢሲኒያ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች በአሉን ተደስተው እንዲውሉ ታሳቢ ያደረገ የማዕድ ማጋራት ተግባር አከናውኗል ብለዋል።
የብልፅግና መንግስት ሰው ተኮር ነው ያሉት አቶ አብዱልበር መሰል በጎ ተግባር ለማከናወን ፍቃደኛ ከሆኑና ማህበራዊ ሃላፊነታቸው ከሚወጡ ተቋማት ጋር በመተባበር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመላክተዋል ፡፡
በዛሬው ዕለትም ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ላደረገው ለአቢሲኒያ ባንክ ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
የአቢሲኒያ ባንክ ወልቂጤ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድምአገኝ አበበ እንደገለፁት ባንኩ በወልቂጤ ከተማ ሁለት ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አውስተው መስቀልን ምክንያት በማድረግ ዘንድሮን ጨምሮ ለሶስተኛ ጊዜ የማዕድ ማጋራት ተግባሩን አከናውኗልም ብለዋል።
በዛሬው እለትም 300 ሺህ ብር የሚጠጋ ገንዘብ በመመደብ ለ50 አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች በአሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ያስችላቸው ዘንድ የማዕድ ማጋራት ስራው ተስርቷል ነው ያሉት።
ባንኩ ማህበራዊ ሃላፊነቱ የመወጣት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት የወጣት ዘርፍ ተወካይ አቶ ዘመዴ በቀለ ፅ/ቤቱ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘርፎች በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን አስታውሰው የአቅመደካሞች ቅድመልየታ በማድረግ ከአቢሲኒያ ባንክና ከከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ጋር በመቀናጀት የማዕድ ማጋራት ተግባሩን አከናውኗልም ብለዋል።
በእለቱ ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖች በበኩላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በአሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ድጋፍ ላደረጉላቸው አካላት አመስግነዋል።
ዘጋቢ፡ ሚፍታ ጀማል- ከወልቂጤ
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ ያደርጋል – የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ