ፍቅሩንና ወዳጅነቱን የሚገልፅበት በጎ ሥራ በበዓላት ቀናት ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

በኣሪ ዞን በመስጅደ ሠላምማዕድ ማጋራት መርሀግብረ ተካሄደ፡፡

በሁሉም የእምነት ተቋማት አስተምህሮ ስለ ሠላም፣ አንድነትና አብሮነት ብሎም የተቸገሩትን መርዳትና መደገፍ የፈጣሪ ትዕዛዝ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ ይህንን በጎ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል ይገባል ሲሉ የመርሀግብሩ አስተባባሪ አቶ ይማም ስዒድ ተናግረዋል ።

በጂንካ ከተማ የሠላም መስጅድ ኢማም ሸህ እንዲሪስ አህመድ በጎ ሥራ ሁሌም የሚተገበር እንጂ በዓላትን ጠብቀን ብቻ የምናደርገው ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡

ይህ በማድረጋችን ከአላህ ወይም ከፈጣሪ በረከትን እናገኛለን ያሉት ኢማሙ የ2017 ዓ.ም 1499ኛው መውሊድ በዓል ታሳቢ ተደርጎ ስለአብሮነትና አንድነት መገለጫ የሆነው ማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በመስጅዱ ተግባራዊ መደረጉን ገልፀዋል።

በማዕድ ማጋራት የተካፈሉ አካላትንም አመስግነዋል ።

ዘጋቢ:  ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን