የትምህርት ቁሣቁስ ድጋፉ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ”ፍሬንድስ ኦፍ ሆመቾ ” የሆመቾ ተወላጆች በጎ አድራጊ ማህበር የተደረገ ነው።
አቶ አረጋ በዶሬ የፍሬንድስ ኦፍ ሆማቾ ግብረ-ሰናይ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ ድርጅቱ በተለያዩ መሠረተ-ልማት ሁነቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ነው ብለዋል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ለጤና አገልግሎት የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የትምህርት ቤቶች እድሳትና ውሃ መሥመር ዝርጋታ ሥራዎች በሰፊ ማከናወኑን ተናግረዋል።
በዕለቱም ከሆማቾ ከተማ አስተዳደርና ጊቤ ወረዳ ለተወጣጡ ለ3 ሺህ አቅመ-ደካማ ተማሪዎች የደብተርና ብዕር ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች አበርክቶ ጉልዕ በመሆኑ በመንግሥት ልታገዙ እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የሆማቾ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ምስጋና አለሙ ናቸው።
ተማሪዎች በተደረገላቸው ድጋፍ በርትተው በመማር ተወዳዳሪና ግንባር-ቀደም እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች ባገኙት የትምህርት ቁሳቁስ መደሰታቸውን ገልፀው፣ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በርትተው እንደሚማሩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- አብርሃም ሙጎሮ ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።