የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያ የዞኑ ሴቶች ንቅናቄ መድረክ  እየተካሄደ  ይገኛል

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያ የዞኑ ሴቶች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የወላይታ  ዞን ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ  ወይንሸት ሞላ የሴቶች ተሳትፎ በጊፋታ በዓል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወትና ለበዓሉ ደምቀት እንደሚሆኑም አስረድተዋል።

ሴቶች በጊፋታ በዓል አከባበር ዙሪያ ለህብረተሰቡ ክፍሎች ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለባቸው  ወ/ሮ ወይንሸት  አሳስበዋል።

በየአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎች እና የቱሪስት መዳረሻዎችንም ለዓለም የማስተዋወቅ ስራ መስራት እንደሚገባና  የወላይታን ባህል፣ ታሪክንና ቋንቋን ለሌሎች ለማስተዋወቅም ሴቶች ሚና የጎላ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የወላይታ ዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ሃብቴ በበኩላቸው ጊፋታ በዓል ከሃይማኖታዊ በዓል ጋር የማይገናኝ መሆኑንም አንስተዋል።

የወላይታ ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅና በህሉን ተደራሽ ለማድረግ የሴቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጊፋታ በዓል የደስታ፣ የፍቅር፣ የሠላም እና የተጣሉት የሚታረቁበት የእርቅ በዓል እንደሆነም አመላክተዋል።

የወላይታ ዞን ሴቶች ሊግ ኃላፊ ወ/ሪት ድርሻዬ በለጠ በዓሉን ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ለማክበር ሴቶች የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መውጣት አለብን ብለዋል።

ዘጋቢ፡ በቀለች  ጌቾ – ከዋካ  ጣቢያችን