ሀዋሳ፡ 28/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) መንግሥት በህዝቦች መከከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና የህዝቦች መተማመን እንዲኖር ምክክርን ባህል ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገልጸዋል:፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ስራውን ከተመራጮችና ከመንግስት ባለድርሻ አከላት ጋር ቀጥለዋል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች አካታችነት፣ ግልፀኝነትን፣ አሳታፊነትንና ተዓማኒነትን መሰረት በማድረግ ለምክክሩ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንደሻው ጣሰው፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
2ኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
የሚገነቡ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ከተሞችን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ውብና ምቹ ለማድርግ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ሥርዓት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ አሳሰበ