ሀዋሳ፡ ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከሕዝቡ የሚነሡ የመልካም አስተዳደርና የልማት ችግሮችን በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ወረዳ የሕዝብ ተወካዮች ገለጹ፡፡
ሕብረተሰቡን ቀርቦ የማናገርና አስፈፃሚውን አካል ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል፡፡
ህዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በሂደት ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ የሕዝብ ተወካዮቹ ተናግረው፥ በኑሮ ውድነት፣ በሠላምና ፀጥታ፣ በፕሮጀክቶች መጓተት፣ በመሠረተ ልማት ግንባታና በለሎችም ችግሮች ዙሪያ ለመፍትሔ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
የቃቆ ሳውላ ዎሞሮ ዳገት ፈጥኖ እንዲያልቅ የፌደራልና የክልል መንግሥት ትኩረትን ይሻል ያሉት የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ የኮይቤ ሴሮ ወንዝ ድልድይ በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲገባ መወሰኑን ተናግረዋል፡፡
የመንገድ ልማቱ የእናቶችና የህፃናትን ህይወት በመታደግ፣ የወረዳ ቀበሌዎችን ከወረዳውና ከዞኑ እንዲሁም ክልል ከተማዎች ጋር የሚያገናኝ ብቸኛ መንገድ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የወረዳዋ ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።