ሀዋሳ፡ ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉን ነባር ብሔረሰቦች ባህል እና ወግ የማሳደግ፣ የማስተዋወቅና የመጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚሰራ የደቡብ ምእራብ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኮ ተናገሩ።
የምክር ቤቱ 2ኛ አመት 3ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ በቴፒ ከተማ እያካሄደ ነው።
የደቡብ ምእራብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት 2ኛ አመት 3ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤው አቶ መቱ አኮ እንደተናገሩት፥ በክልሉ የሚገኙ 13 ነባር ብሔረሰቦች ቋንቋቸውን ባህላቸውን ታሪካቸውን የማሳደግ የማስተዋወቅ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፥ ይኸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ምክር ቤቱ በተለይም በክልሉ ህዝቦች ውስጥ አልፎ አልፎ የሚታዩ አለመግባባቶችን በሰላምና በአብሮነት መንፈስ መፍታት እንዲያስችል የግንዛቤ መድረኮችን ከማመቻቸት ባለፈ፥ ነባር ባህላዊ የግጭት አፈታት ሂደቶችን በማጠናከር በአከባቢው ቋንቋዎች ባሉ ኤፍ ኤሞች በመጠቀም የሰላም ግንባታዎች ላይ እየተሰራም እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
እንዲሁም በክልሉ ላሉ ወጣቶች በፌደራሊዝም እና በህገመንግስት ዙሪያ ግንዛቤ እንዲያገኙ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ያካሄደውን የምክር ቤቱን የ2ኛ አመት 2ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ያጸደቀ ሲሆን፥ የ2016 የምክር ቤቱን እቅድ ክንውን እና የ2017 እቅድ ለምክር ቤቱ አካላት ቀርቦ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ