ሀዋሳ፡ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የጊፋታ ዕሴቶች ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እንደሚከበር የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር አስታውቋል::
በ2017 ዓ.ም የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል ዘንድሮ በመስከረም 12 ላይ ይከበራል።
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለጹት የጊፋታ በዓል ሕዝባዊና በጉጉት የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“የጊፋታ ዕሴቶች ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል እንደሚከበር አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በአሉን ለማክበር ቅንጅታዊ አሠራር እንደሚጠይቅ አስረድተዋል።
በወላይታ ብሔር ዘንድ ጊፋታ የአሮጌው ዓመት ማብቂያ እና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡
በዓሉን የማስተዋወቅ ሥራ በሚዲያ በመታጀብ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሕዝቡ የራሱን ማንነት መገለጫ መሆኑን በማመን ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እስከ በዓሉ ዕለት ድረስ ለበዓሉ ድምቀት የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል ።
የጊፋታ በዓል አከባበር ምክንያት በማድረግ የሚከናወኑ ሁነቶች ዙሪያ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል ።
አቶ ተሾመ ሃብቴ የወላይታ ዞን ባህልና ቱርዝም መምሪያ ኃላፊ የዘንድሮው ጊፋታ በመስከረም 12/2017 ዓ.ም በድምቀት እንደሚከበር አንስተው በአሉ ባህልንና ሐይማኖትን ጋር የማይጻረር የወላይታ ሕዝብ ማንነት መገለጫ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ በቀለች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ