በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና በዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ልዑክ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታን አስጀመረ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እና በኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የተመራ ልዑክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዊ ህዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ አስጀምሯል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በታርጫ ከተማ ለአምስት አቅመ ደካሞች ዘመናዊና ሙሉ የቤት ቁሳቁሶች የተሟሉላቸው አምስት ቤቶች እንደሚገነባ አስታውቋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከGGGI ከተሰኘ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለቤቶቹ ግንባታና ለቤት ቁሳቁስ ግዥ ከ12 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር በላይ በጀት እንደተመደበ የኢፌዲሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አብራርተዋል።

በክልሉ እየተከናወነ የሚገኝ የበጎ አገልግሎት ተግባራት በርካታ ዘጎችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፤ የተጀመሩ በጎ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በመርሃግብሩ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ እታገኝ ዘነበ – ከዋካ ጣቢያችን