የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ለማስቻል መንከባከብ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ዶክተር አማረች በካሎ አሳስበዋል

የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ለማስቻል መንከባከብ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ዶክተር አማረች በካሎ አሳስበዋል

የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ ያካሄዱት በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኢንዱስትሪና ማዕድን ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር አማረች በካሎ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከተጀመረ ወዲህ በአካባቢ አየር ጥበቃ ላይ ከፍተኛ ጥቅም እያገኘን ነው ብለዋል።

ዘንድሮም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበረ በሚገኘው የተከላ መርሃግብር በማረቃ ወረዳ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በመሳተፋቸው አመስግነዋል።

በተካሄደው የተከላ መርሃግብር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ቢሆንም የተተከሉ ችግኞች ተጠብቀው ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ ለማስቻል ደግሞ ከአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ሀላፊነት የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ከማህበረሰቡ ባለፈም የዘርፉ ተቋማትም የጥበቃና እንክብካቤ ተግባራትን በትኩረት መስራት እንደሚገባም ዶክተር አማረች አሳስበዋል።

ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን