እንደሀገር በተለያዩ ዝግጅቶች ችግኝ የመትከልና የማልማት ባህል ከጊዜ ወደጊዜ ልምድ እየሆነ በመምጣቱ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በኣሪ ዞን በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ላይ በክብር እንግድነት የተሳተፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያን አረንጓዴ ማልበስ ከፖለቲካ በዘለለ በዓለም ደረጃ በመልካም ተግባር ማስተዋወቅ በመሆኑ መርሀግብሩን በተገቢው ማከናወን ይገባል ብለዋል።
በኣሪ ዞን በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ላይ የተሳተፉ የሕብረተሰብ ክፍሎችም እየተተከሉ ያሉትን ዘርፈብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚያበረክቱም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ዳኜ ጥላሁን – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ