ሀዋሳ፡ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር እየተከናወነ ነው፡፡
እንደ ሀገር በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሀግብር በምስራቅ ጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ በደማቅ ስነስርዓት በመከናወን ላይ ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ታጁ ነሥሩ፣ የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዶ አህመድ፣ የከተማው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሳሙኤል ማርቆስን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የዞንና የከተማው አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ነዋሪዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ እስከ ምሸቱ 12 ሰአት እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ትግስት ተሾመ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ