ዛሬ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም “የሚትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ሀገር ዓቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ አካል የሆነው በቡርጂ ዞን ችግኝ እየተተከለ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ በዘንድሮ ለ5ኛ ዓመት እየተካሄደው ያለው ችግኝ ተከላ በቡርጂ ዞንም ችግኝ እየተተከለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከሚተከሉ ችግኞች መካከል የፍራፍሬ፣ የጥላ ዛፎችና ሌሎችም እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው አንድ ግለሰብ እስከ አመሻሽ 20 ችግኞችን መትከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በችግኝ ተከላ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳኜ ህዶ ህብረተሰቡ ማለዳ በመውጣት አገራዊ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን እያካሄደ እንደሚገኝ አንስተው እንደ ቡርጂ ዞንም በሁሉም አካባቢዎች ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ እየተከ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በዞኑ ምቹ የአየር ፀባይ እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መተከላቸው ፋይዳው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚረዳ በመሆኑ ተከላውን በማሳካት የሚጸድቁትን በመከታተል መንከባከብ እንደሚገባ የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: ዮስፍ ቶልኬ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ