“የምትተክል ሀግር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኦሞ ዞን የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ በ6 ጣቢያዎች የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የችግኝ ተከላው በወረዳው በሲሳይ እርሻ ሳይት ጣቢያ 1 እና 2፣ በናሮጎይ፣ በGIZ-ጣቢያ፣ በጤና ጣቢያ እንዲሁም በካንጋቲን ሆስታል እየተተከለ ይገኛል፡፡

በመርሃ-ግብሩ የዞኑ አመራሮች፤ የወረዳው አመራርን ጨምሮ መላው የወረዳው ማህበረሰብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን