ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “የምትተክል ሀገር፡ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በደቡብ ኦሞ ዞን ማሌ ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡
በመላው ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በወጣው እቅድ መሰረት በማሌ ወረዳ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
መርሐ ግብሩን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ ከዞኑ በመጡ ደጋፊ አመራሮች ጋር በመሆን በአሸከር ቀበሌ በመገኘት እያካሄዱ ነው።
በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በወረዳው በተለዪ 20 ቦታዎች ተከላው እየተካሄደ ይገኛል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ