ሀዋሳ፡ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዳውሮ ዞን በ181 ቀበሌያት የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በአንድ ጀንበር በዞኑ ሊተከል የታቀደው በ99 መትከያ ቦታዎች የመረጃ ቋት መዘጋጀቱን የዳውሮ ዞና ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ በተላ በየነ ገልፀዋል።
ለተከላ በተመረጡ ቦታዎች የችግኝ ፅድቀት መጠንን ለማሳደግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በማዋቀር እንዲጠበቁ ለማስቻል ታቅዶ እየተሠራበት ነው ብለዋል።
በተከላው አባቶች፣ ሴቶች ወጣቶችን ጨምሮ የተለያዩ ማህበራ መሰረቶች ተሣታፊ ሆነዋል።
አሁን ላይ በዞኑ ሊተከሉ በታቀደባቸው 181 ቀበሌያትም የችግኝ ተከላ እየተካሄደ እንደሚገኝ አቶ በተላ ገልፀዋል።
በማረቃ ወረዳ ካነጋገርናቸው በተከላው ከተሣተፉት መካከል ወ/ሮ ጌታቸው ላንጋና እና አየለች ኡማ ችግኝ መትከል ለአካባቢያችን አየር ፀባይ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበን በየዓመቱ እየተከልን ቆይተናል ብለዋል።
ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው በአንድ ጀንበር በየግላቸው ከ15 በላይ ችግኞችን በመትከላቸው ደስተኞች መሆናቸውንም ገልፀዋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የአርሶ አደሩን የመሬት ሀብት ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር አርሶአደሩ የፋይናንስ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የእናቶች ጤናና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2018 ባጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መድረክ በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ ይገኛል
የከተማ አስተዳደሩ ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽህፈት ቤት ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ