የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ አመት ስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚዛን አማን ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ጌድዮን ኮስታብ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቶች የዞኑ ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫ ናቸው።
በየደረጃዉ የሚገኙት ምክር ቤቶች በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና በመንግሥት አሰራር ዉስጥ የሕዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ተግባራትን በማከናወን ህገ-መንግስታዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉም ነዉ ዋና አፈ ጉባኤዉ የጠቆሙት።
ምክር ቤቱ የሚወጡ ህጎችን በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች በተገቢው እንዲተገበሩ አስፈፃሚ አካላትን በመከታተል በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው የዞኑን የአስተዳደር ምክር የ2016 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2017 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል።
በመጨረሻም በዞኑ በቅርቡ የተዋቀሩትን የሸኮ እና የቢፍቱ ከተማ አስተዳደሮች የመዋቅር ጉዳይ በጉባኤ ቀርቦ የሚፀድቅ ሲሆን የተለያዩ ሹመቶች እንደሚኖሩም የጉባኤው መርሃ-ግብር ያሳያል።
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።