ሀዋሳ፡ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለሚዲያ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ነው።
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉጃ ጉሜ በዚህ ወቅት እንዳሉት ወደ ተቋሙ አዲስ የተቀላቀሉና ነባር ባለሙያዎች ወቅታዊ የሙያ ነክ ስልጠናዎችን በመውሰድ በዕውቀት እና በክህሎት የዳበሩ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተግባቦት መመምህር ዕጩ ዶ/ር ተስፋዬ አለማየሁ በበኩላቸው የሚድያ ዘርፉ ተለዋዋጭ እና እያደገ በመጣው ዓለም ልክ ባለሙያውም ራሱን በተሻለ ዕውቀት እና መረጃ የታጠቀ መሆን እንዳለበት መክረዋል።
ትክክለኛ እና ወቅታዊ እንዲሁም ሚዛናዊ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ለማድረስ በሚዲያ ዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለማለፍ ተሽሎ መገኘት ይጠይቃል ያሉት ዕጩ ዶ/ር ተስፋዬ ሚዲያዎች ከቴክኖሎጂ ጋር መጓዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ከደን ምንጣሮ የፀዳ ቡና በማምረት አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እተየሰራ ነው
የሣውላ ከተማ ህዝብ ምክር ቤት አባላትና ከፍተኛ አመራሮች የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኙ
ክርስቲያን የቡና ግብይትና ሁለገብ የሕብረት ሥራ ማህበር በቡና ጥራት ዙሪያ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑን ገለፀ