“ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል የኤግዚቢሽንና ባዛር ንቅናቄ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል የኤግዚቢሽንና ባዛር ንቅናቄ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ ንቅናቄ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች እና አምራች ኢንተርፕራይዞች እየተሣተፉ ይገኛሉ።
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀየሰችው ሀገራዊ ፖሊሲ የአምራች ኢንዳስትሪ ዘርፉን ለማጠናከር በተሠራው ሥራ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ልማት ባንክ ጋር ትስስር በመፍጠር የክህሎት ስልጠና መሰጠቱንም ገልጸዋል።
ይበልጥ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ሐሣብ አመንጪነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ዕሳቤ ለዜጎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀመታን የሚያጎናጽፍ መሆኑን ገልጸው ክልሉ ያለውን ሐብት ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተጀመረውን ሥራ አጠናክሮ መቀጠል እና ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንደሚጠበቅባቸውም የተናገሩት አቶ አለማየሁ ለኢንዱስትሪው አስፈላጊውን ግብአት ከማምረት አኳያ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመቅረፍ በትኩረት እሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
ንቅናቄው የገቢ ምርቶችን ለመተካትና ወጪ ምርቶችን ለማሣደግ ጠቄመታው የጎላ ስሆን ከ70 በላይ ኢንዳስቲሪያልስቶች እና አምራች ባለ ሐብቶች በተዘጋጀው ባዛርና ኤግዚቢሺን ላይ ተሣታፊ ናቸው።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው- ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
2ኛ ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
የሚገነቡ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ከተሞችን ለነዋሪዎች ጽዱ፣ ውብና ምቹ ለማድርግ በቆሻሻ አወጋገድና አያያዝ ሥርዓት ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ አሳሰበ