የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፤ ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር “የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል” በሚል መሪ ቃል የኤች አይ ቪ ኤድስ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ወልደ እንደተናገሩት፤ በሀገር አቀፍ ብሎም በከተማ አስተዳደሩ የተጀመረውን የብልጽግ እውን ለማድረግ ጤናማ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባል።
በበጀት አመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ተቋሙ በርካታ አመርቂ የጤና ተግባራት ማከናወኑን አመላክተው በቀጣይ ተቋሙ የኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከልና መቆጣጠርን ጨምሮ በንቅናቄና በዘመቻ የጤና ተግባራት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በአሪ ዞን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስፋው ዶሪ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ጤና ለሁሉም ተግባር መሠረት ቢሆንም በከተማ አስተዳደሩ አምራቹን የማህበረሰብ ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃ ያለውን የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና የመቆጣጠር ሥራው እየተዘናጋ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የጤና ሥራን ጨምሮ ከተማ አስተዳደሩ በ100 ቀናት ዕቅድ በሚያከናውናቸው ተግባራት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ትኩረት ተሰጥቶበት ይሰራል ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ 100 ቀናት ለሚያከናውናቸው ሁሉ አቀፍ ተግባራት ስከታማነት ተቋማትና ግለሰቦች የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመድረኩ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠርን ጨምሮ የተቋሙ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
ዘጋቢ፡ መልካሙ ቡርዝዳቦ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ