“እናንተ ባበረከታችሁት አስትዋፅኦ የሰላምና የልማት ሥራዎችን እየሰራን በመሆኑ በክልሉ ስም ምስጋና ይገባችኃል” – አቶ እንዳሻው ጣሰው
ሀዋሳ: ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በክልሉ የሚገኙ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበዋል::
ርእሰ መስተዳድሩ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የታክስ ህግ ተገዥነት የንቅናቄ እና የግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት መርሀግብር ላይ ተገኝተው ለታማኝ ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል::
“ታማኝ ሆናችሁ ባበረከታችሁት አስተዋፅፆ የሰላም የልማት ሥራዎችን እየሰራን በመሆኑ በክልሉ ስም ምስጋና ይገባችኃል” ነው ያሉት ርእሰ መስትዳድሩ::
በዘርፉ ያሉ የገቢ ሠራተኞችም አድልኦ የሌለበት ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ያሳሰቡ ሲሆን በቀጣይም ለኢትዮጵያ ብልፅግና ተግተን በጋራ እንሠራለን ብለዋል ርእሰ መስተዳድሩ::
በመርሀ ግብሩ ላይ ግብርን በታማኝነት በመክፈል የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት የቻሉ ግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ
በሀዲያ ዞን ከ8መቶ 50ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸው ተገለፀ