በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ፣ የማዕድን ሚኒስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝን ጨምሮ የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎችና ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በአገሪቱ ከሚታረሰው ማሳ 43 በመቶ ማለትም 7 ሚሊየን ሄክታር መሬት በአሲዳማነት የተጠቃ ነው።
በ2016/17 ምርት ዘመን 100 ሺህ ሄክታር መሬት በኖራ ለማከም ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ለዚህም 1.5 ቢሊየን ብር ከመንግሥትና ከልማት አጋሮች እንደሚያስፈልግ የግብርና ሚኒስትሩ አመላክተዋል።
የግብርና ኖራ አቅርቦትና ስርጭት ማስፈጸሚያ ሰነድ በኢንቨስትመንትና የግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት በዶክተር ሶፊያ ካሳ ቀርቧል።
ሰነዱን መነሻ በማድረግ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መሪነት ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በኢንቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ወደስራ ባልገቡ ባለሀብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የከተማው አስተዳደር አስታወቀ
በፍየልና በግ ማሞከት ተግባራት ላይ በመሰማራታቸው ተጠቃሚ መሆናቸውን በሀዲያ ዞን አንዳንድ የሶሮ ወረዳ ሴቶች ተናገሩ
የገጠር ተደራሽ መንገድ የበርካቶችን የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እየፈታ መሆኑ ተገለጸ