በተያዘው የበልግ ወቅት ከ38 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን መታቀዱን የኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ
የወረዳው አርሶ አደሮችም የእርሻ ዝግጅት ጨርሰው ምርጥ ዘርና ግብአት መውሰድ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የሳርማሌ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ፣ የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊና የኢኮኖሚና መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዜና ዘካርያስ ለዘንድሮው የበልግ እርሻ 38 ሺህ 552 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዷል ብለዋል፡፡
የእርሻ ዝግጅት ከ1ኛ አስከ 3ኛ ድረስ የተጠናቀቀ ሲሆን አፈጻጸሙም 95 በመቶ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
በወረዳው የተለያዩ የሰብል ዓይነቶች የሚመረቱ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 70 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር፣ 799 NPS እና 220 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ቀርቦ ሥርጭት መጀመሩን ተናግረዋል።
የደርባ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማክሮብ ስዩም በበኩላቸው በቀበሌያቸው በበልግ ወቅት በቆሎ በስፋት እንደሚመረት ገልጸው የምርጥ ዘርና ግብአት አቅርቦት ተመጣጣኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አርሶአደር አሜሪካን ከበደና ከበደ ከፋ የደርባና ትፋቴ ቀበሌ አርሶአደሮች ሲሆኑ በዘንድሮው የበልግ ወቅት በፀጥታ ስጋት ምክንያት ትቷቸው የነበሩ አከባቢዎችን ጭምር በዘር ለመሸፈን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ምርጫ መላኩ- ከይርጋ ጨፌ ቅርንጫፍ
More Stories
ስፖርት በአንድ አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከማቀራረቡም በተጨማሪም ለአንድ አካባቢ ሰላም መስፈን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ
አምረፍ ሄልዝ አፍሪካ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለበርካታ ዓመታት የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ
ከእርሻ መሬት መጠቀሚያ ግብር 20 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን የጎምቦራ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ ቤት አስታወቀ