በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ የሚፈልጉ በመሆናቸው ለዘርፉ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተገለፀ
ሀዋሳ፤ የካቲት 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ የሚፈልጉ በመሆናቸው ለዘርፉ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ጠየቁ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወላይታ ዞን ከህዝቡ ጋር ባደረጉት መድረክ የተነሱ ጉዳዮች በተመለከተ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር ውይይት አካሄደዋል።
የፌደራልና የክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በየደረጃው ከመራጩ ህዝብ ጋር በተደረገው መድረክ ህዝቡ ያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን አንስተዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦችን አስመልክተው የህብረተሰቡ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና መሰል ጥያቄዎችን በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን ህዝቡ ያነሳቸው አንዳንድ መሠረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልጉ በመሆናቸው ከፌደራልና ክልል መንግስት ጋር በመተባበር ለመስራት ቃል ገብተዋል።
የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የተለያዩ ዕቅዶች በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።
የህዝቡን አስተማማኝ ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በዞኑ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሰራት ላይ መሆናቸውንም አብራርተዋል ።
የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ህዝቡን እያማረረ ያለ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ተገቢ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አክለዋል።
በፌዴራል እና በክልሉ በጀት ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያት የቆሙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ትኩረት ተሰጥቶ መጠናቀቅ አለበት ብለዋል።
የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የልዑካን ቡድን መሪ አቶ መለሰ መና በየደረጃው ከመራጩ ህዝብ ጋር በተደረገው መድረክ የመብራት፣ የመንገድ፣ የውሃና ጤና ተቋማት ተደራሽነት ጋር የተነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልጉ ናቸዉ ብለዋል።
በዞኑ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች ናቸዉ በማለት ይህም በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ሥራ አጥነትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ለዘርፉ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የዞኑ ምክርቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ወ/ሮ ወይንሸት ሞላ በበኩላቸው ህዝቡ የሚያነሳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በየደረጃው ተገቢ ምላሽ ለመስጠት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
በቀለች ጌቾ፡ ከዋካ – ጣቢያችን

 
                 
                                         
                                         
                                         
                                        
More Stories
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግስትን ወጪ ከማዳን ባሻገር ለህሊና እርካታ የሚሰጥ ተግባር መሆኑ ተነገረ