የጎፋ ዞን የሕዝብ እንደራሴዎች የመራጭ ተመራጭ መድረክ አካሄዱ

የጎፋ ዞን የሕዝብ እንደራሴዎች የመራጭ ተመራጭ መድረክ አካሄዱ

ሀዋሳ፡ የካቲት 21/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በዑባ ደብረፀሐይ ወረዳ ምርጫ ክልል በበቶ ከተማ አስተዳደር የፌዴራል እና የክልል ተመራጮች ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩም የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች፣ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣ የተጀመሩ የፌደራልና የክልል ፕሮጀክቶች ወቅቱን ጠብቀው በመጠናቀቅ ለህዝቡ ጥቅም መስጠት እንዳለባቸው፣ የአከባቢውን የመሬትና የመልማት እምቅ አቅም ለመጠቀም በስፋት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማምረት እንዳለባቸው የኤፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጋሻያለው ጋለ አሳስበዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ በበጀት ዓመቱ በስድስት ወር በተሰሩና ቀጣይ በሚሰሩ ተግባራት ማለትም በሰላምና በፀጥታ ሥራዎች፣ በኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ በማህበራዊና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም የህዝብ ተመራጮቹ ከህዝቡ ለተነሱ ጥያቄዎችና የልማት ፍላጎቶች ምላሽና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ ፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት