የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጡ 7 የተለያዩ አዋጆችና ደንቦችን ተቀብሎ አጸደቀ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጡ 7 የተለያዩ አዋጆችና ደንቦችን ተቀብሎ አጸደቀ

ሀዋሳ፡ የካቲት 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም የነበሩ አዋጆችና ደንቦችን በማሻሻል ከአዲሱ ክልል አደረጃጀት ጋር ማጣጣም አስፈላጊ በመሆኑ፥ የክልሉን ህዝብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ እንዲያስችል የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጡ 7 ረቂቅ አዋጆችና ደንቦችን ተቀብሎ አጽድቋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ፥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህግ፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር በድጋሚ ለመወሰን የወጡ የ7 መስሪያ ቤቶችን ማቋቋሚያ አዋጅ ከክልሉ ህገ መንግስት ጋር የተጣጣመ በማድረግ፥ ለምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጆችን እንዲያጸድቅ የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል።

በዚህም መሠረት:-

1 የፍርድ ቤቶች አዋጅ፣

2 የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ፣

3 የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ፣

4 የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን አዋጅ፣

5 የፍትህ ቢሮ አዋጅ፣

6 የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ፣

7 የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ፥ የቀረበለትን 7 ረቂቅ አዋጆች ገንቢና ጠቃሚ የማስተካከያ አስተያየቶችን በማከል በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቋል።

ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ