በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ያሉ መረጀዎች ፍሰት ወጥነት ያለቸው እንዲሆኑ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ የካቲት 15/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ያሉ መረጀዎች ፍሰት ወጥነት ያለቸው እንዲሆኑ በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ከተጠሪ ተቋማቱ እና ከክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የህዝብ ግንኙትና ኮሚኒኬሽን ጋር የመረጀ አያያዝና ተደራሽነት ሥርዓት ለማስፈንና ለማጠናከር የሚያግዝው ፎረም መስርቷል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ጌጡ እንደገለጹት፥ ፎረሙ በከፍተኛ ሀብት የሚተገበሩ የውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶችን መረጃዎች ወጥነት ባለው መልኩ ተደራሽ ለማድረግ አቅም ይፈጥራል።
የተጠሪ ተቋማትም ሆኑ የክልል የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ተአማኒነት ያለቸውን መረጀዎች ለህብረተሰቡ ማድረስ እንደሚጠበቅባቸው አስገዝበዋል ።
በየደረጀው የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በመከታተል ህብረተሰቡ መረጃ እንዲኖረው ከማድረግ በተጓዳኝ ለፕሮጀክቶቹ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያደርግ የፎረሙ አባለት ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚጠበቅበት አቶ ጌትነት አመላክተዋል ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ኃይሉ በበኩላቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን በህዝብና በመንግሥት ሀብት የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ለህብረተሰቡ የማሳወቅና የመከታተል ተልዕኮውን በተገቢው እንዲወጣ የፎረሙ መመስረት አጋዥ እንደሚሆን ተናግረዋል ።
ከፕሮጀክቶች አፈጻጸም ጋር ተያይዘው ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎችም ግልጽነትን የሚፈጥሩ መረጃዎችን በቅርበት ተደራሽ ማድረግ ሌላኛው የፎረሙ ዓለማና ተልዕኮ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የፎረሙ አባለት ዘመኑን የሚመጥን ሳይንሳዊ የሆነ የተግባቦት እውቀት የተላበሱ መሆን እንደሚጠበቅበትም አቶ ማሙሻ አስረድተዋል ።
በፎረሙ ደንብ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ ፎረሙ በይፋ ተመስርቷል ።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ