ለረሃብ እና ለተመጣጠነ የምግብ እጥራት ተጋለጭ የሆኑ ህጸናትን ተደራሽ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ይፋ ሆነ

ለረሃብ እና ለተመጣጠነ የምግብ እጥራት ተጋለጭ የሆኑ ህጸናትን ተደራሽ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ይፋ ሆነ

ሀዋሳ፡ የካቲት 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ለረሃብ እና ለተመጣጠነ የምግብ እጥራት ተጋለጭ የሆኑ ህጸናትን ተደራሽ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ዘመቻ ይፋ ሆኗል።

ዘመቻው በወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል አስተባባሪነት የተለያዩ አጋርና ለጋሽ ድርጅቶችን እንዲሁም የመንግሥታትን አቅም በማሰባሰብ በህጸናት ላይ የሚደርሰው ረሃብና የተመጣጠነ የምግብ እጥራት ችግር “Enough” ወይንም ይብቃ! በሚል መሪ ሀሳብ በ27 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ለሦስት ዓመት የሚተገበር ነው ተብሏል።

በወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሊላን ዶድዞ እንገለጹት፤ ለዘመቻው ተግበራዊነት 1.7 ቢሊየን የአሜሪካን ዶለር በጀት ያስፈልጋል።

በምሥራቃዊ፣ ምዕራባዊ እና ደቡባዊ የአፍሪካ አገሮች በሚፈጠሩ ግጭቶች፣ ድርቅ እና መፈናቀል ሳቢያ በርካታ ቁጥር ያለቸው ህጸናት ለረሃብና ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት ተጋላጭ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

“በአፍሪካ ህጸናት ለይ የሚደርሰው ረሃብና የተመጠነ የምግብ እጥረት ችግር በቃ”! የሚለው ዓለም አቀፍ ዘመቻ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም አካላት የተቀናጀ ድጋፍና ርብርብ እንዲያደርጉም ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል።

የኢፌዴሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የዓለም አቀፍ ዘመቻውን በሸራተን አዲስ በይፋ አስጀምረዋል።

ለዘመቻው ስኬታማነት የኢትዮጵያ መንግስትና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግም ዶክተር ኤርጎጌ አረጋግጠዋል።

የሴቶችንና የህጸናትን የሥነ-ምግብ ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ፖሊሲዎችንና ፕሮግሞችን የኢትዮጵያ መንግሥት በከፍተኛ ትኩረት ገቢራዊ እያደረገ እንደሚገኝም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።

ለዚህም የሌማት ትሩፋት ፕሮግራምን በአስረጅነት በማንሳት የህጸናቱን ልየታ ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ እንደሚሠራም ዶክተር ኤርጎጌ ጠቁመዋል።

“በህጸናት ለይ የሚደርሰው ረሃብና የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ችግር በቃ”! በሚል ይፋ በሆነው በዚሁ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ ዘመቻ የወርልድ ቪዥን ኢንተርናሽናል ከፍተኛ አመራሮች፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሰደሮች፣ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች አጋሮችና ለጋሽ ድርጅቶች ተገኝተዋል።

ዘመቻው ከፈረንጆቹ የዘመን ቀመር ከ2024 እስከ 2026 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በችግሩ ተጋላጭ የሆኑ 6 ሚሊዮን ህጻናትን በሁሉም የአገሪቱ አከባቢዎች ተደራሽ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ