የውሃና ኢነርጂ ኢግዚቢሽን ስኬታማ ሆኖ እንዲጠነቀቅ ጉልህ አስተዋፅኦ ለባረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጠ
ሀዋሳ፡ የካቲት 12/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የውሃና ኢነርጂ ኢግዚቢሽን ስኬታማ ሆኖ እንዲጠነቀቅ ጉልህ አስተዋፅኦ ለባረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር “የውሃ ሀብታችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ ቃል ከነሐሴ 12 ቀን 2015 እስከ መስከረም 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ ሀገር አቀፍ ኢግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም ባዘጋጀበት ወቅት ለስኬታማነቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በወርሃ ነሐሴ 2015 ዓ.ም ባካሄደው አገር አቀፍ የውሃ ኢግዚቢሽን በመጠጥ ውሃ፣ በኢነርጂ እና በውሃ አስተዳደር ዘርፎች እንዲሁም የሚኒስቴሩን ተጠሪ ተቋማት አገልግሎቶችን ለጉብኚዎች ያቀረበበት ነበር።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ በምስጋናና እውቅና ሥነ ስርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ኢግዚቢሽኑ በርካታ እውቀትና ስኬት የተገኘበት ነው።
ኢግዚቢሽኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታቸውና ተጠሪ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ላሉ ጎብኚዎችና መሪዎች ማሳየት የታቸለበት እንደነበረም አስታውቀዋል።
የማመስገንና እውቅና የመስጠትን ባህል ማጎልበት ቀጣይ የተሻሉ ሥራዎችን ለመሥራት በዘርፉ የተሰማሩ አካለትን ይበልጥ የሚያበረታታ እንደሆነም ዶክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተናግረዋል።
የሀገር አቀፍ ኢግዚቢሽኑን አጠቃላይ ኩነቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ከፍተኛ አበርክቶ ያደረጉ የሚዲያ ተቋማትን ጨምሮ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች፣ ለተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር አብረው ለሚሠሩ አጋር አከላት የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት አውቅና ተበርክቶላቸዋል።
የኢግዚቢሽን ዝግጅቱ በቀጣይ ጊዜያትም ቋሚነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን ከቻይና ገጠር ልማት ፋውንዴሽንና ከሐመር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረጉ
በሲዳማ ክልል ለተገኘው ሰላም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነበር – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
የአራቱም ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ