አጨቃጫቂና ለብጥብጥ የሚያነሳሱ ትርክቶችን በመተው የሀገራችንን የዕድገት ጉዞ በአብሮነት ማስኬድ እንደሚገባ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ የካቲት 08/2016 ዓ.ም (ደረሬቴድ) አጨቃጫቂና ለብጥብጥ የሚያነሳሱ ትርክቶችን በመተው የሀገራችንን የዕድገት ጉዞ በአብሮነት ማስኬድ እንደሚገባ ተገልጿል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በታርጫ ከተማ የህዝብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ በከተማ አስተዳደሩ በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች የተከናወኑ ተግበራትን ለተሣታፊች ያቀረቡት የከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ የከተማው አስፋልት መንገድ ዲች ያለመሰራትና ግንባታውም አለመጠናቀቅ፣ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ውስንነት፣ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ታርጫ ካምፓስ ግንባታ መስተጓጐል፣ እና መሰል ህዝቡ የሚያነሷቸው የነበሩ ያደሩ ችግሮ በመሆናቸው መፈታት ያለባቸው እንደሆኑ አብራርተዋል።
ለውይይቱ የተዘጋጀው ሰነድ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ያቀረቡት ሲሆን የውይይቱ አስፈላጊነት በሀገሪቱ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ህብረተሰቡ እውቀት ኖሮት በለውጥ ጉዞ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያበረክት ለማስቻል መሆኑን አስረድተዋል።
ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር ሀብትን፣ ማወቅ የመፍጠርና በአግባቡ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑ በሰነዱ የተብራራ ሲሆን ያሉንን ለም መሬት፣ የከበሩ ማዕድናት፣ የሰው ሀይልና ዕውቀትን በመጠቀም የሥራ ባህልንም በማሻሻልና ሠርተን መበልጸግ ይገባል ሲሉም አቶ ኢብራሂም አብራርተዋል።
የበለፀገ ማህበረሰብ በመፍጠር ግጭቶችንና ችግሮችን በውይይትና በሠላማዊ መንገድ መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህም እውቀት ያለው፣ ውጤታማና ሥራ ፈጣሪ የተማረ ዜጋን መፍጠር መሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።
ኢትዮጵያውያን የተሳሰረ ህልውና እና የተጋመደ ማንነት ባለቤት በመሆናችን እርስ በርስ ግንኙነትና ትብብር በማጠናከር ዕድገታችንን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
በተለይም የኋላ ታሪካችን የጭቅጭቅና ብጥብጥ መንስዔ እንዳይሆን በማድረግ አብሮነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው የወል ትርክቶች ማጎልበትና የሚነጣጥል ትርክቶችን ደግሞ ማራቅ እንደሚገባ በሰነዱ ተብራርቷል።
በታርጫ ከተማ የተለያዩ የከተማው የህብረተሰብ ክፍሎች፤ የክልል፣ የዞንና የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ባለስልጣናት በተገኙበት የህዝብ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የምረጡን ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ በኣሪ ዞን ጋዘር ከተማ አካሄዱ
በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ እና በላሃ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የማጠቃለያ ሕዝባዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም ተካሄደ
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን 7 ቀናት ብቻ ቀርተውታል