በሀገሪቱ የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆንና ዘለቄታ ያለው ሠላም እንዲረጋገጥ የወጣቶች ሚና የላቀ ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ
“እኔ ለሀገሬ የሠላም ዘብ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የወጣቶች የውይይት መድረክ በአርባምንጭ ከተማ አየተካሄደ ይገኛል።
በውይይት መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ማዜ ሸቀኔ ፤ በሀገሪቱ የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆንና ዘለቄታ ያለው ሠላም ሰፍኖ ዜጎች በሀገራቸው ተረጋግተው መኖር እንዲችሉ ለማስቻል የወጣቱ ሚና የላቀ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዞኑ እየተስተዋለ ያለውን የወጣቶች ሥራ አጥነት ችግር ከመቅረፍ አኳያም ወጣቱን በተለያዩ የሥራ መስኮች በማሰማራት ራሱንና ሀገሪቱን በሚጠቅም መልኩ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በውይይት መድረክ በርካታ የአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
ዘጋቢ: እንጃ ገልስሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የይርጋጨፌ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን የድጋፍ ሰልፍ አካሄዱ
ሙያዊ ስነ-ምግባር የተላበሰ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው