በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት ዋቆ ትባላለች፡፡

“እናትነት”

በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት ዋቆ ትባላለች፡፡ ከልጅነቷ ጀምሮ የህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት ከፍታ የማሳደግ ህልም ቢኖራትም ነገሮች ባለመመቻቸታቸው ምክንያት ያሰበቸው እንዳልተሳካ ትናገራለች።

ሆኖም ግን ወ/ሮ ትዕግስት የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች 6 ዓመት ሆኗታል፡፡ አሁን ደግሞ ሁለተኛ ልጇን በእርግዝና ወቅት እያለች ለባልደረቦቿ በጨዋታ መልክ ምናልባት የተጣለ ሕፃን ወይም የተቸገረች እናት ልጅ ለመስጠት ከመጣች እባካችሁ አገናኙኝና ከምወልደው ልጄ ጋር መንታ አድርጌ አሳድገዋለሁ ብላ ነበር፡፡

የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ የወሊድ እረፍት ከወጣች በኋላ ታህሳስ 04/2015 ዓ.ም ሴት ልጇን በሰላም ተገላገለች፡፡ ከዚያም ከ2 ወራት በኋላ ባለቤቷ የአንድ ወንድ ሕፃን ልጅ ፎቶ በሞባይሉ አንስቶ ወደ ቤት መጥቶ ስለነበር ማንነቱን እንደጠየቀችው ትናገራለች፡፡ ባለቤቷ ሲያስረዳት ጨለለቅቱ ከተማ በአንድ ደን ውስጥ ተጥሎ የተገኘ ህፃን ነው፤ ሰዎች ሆስፒታል ሲያመጡት የ1 ወር ህፃን ይሆናል፡፡ ሆስፒታል ደግሞ ተቀብለውት 4ዐ ቀናት ሆኖታል አለኝ፡፡ 

አሁን መስከረም ውጥኗ የተሳካ ይመስላል፡፡ የፈለገችውና ቀድማ በአንደበቷ የተናገረችው ቤቷ ድረስ የመጣ ይመስላል፡፡ ከዚያም ባለቤቷን የማሳመን ስራዋን ቀጠለች፡፡ ወ/ሮ መስከረም ህፃኑን ወስዳ ማሳደግ ብትፈልግም  ባለቤቷ መጀመሪያ ላይ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ግድ የለሽም ይከብድሻል ቢላትም ድካሙንም ኃላፊነቱንም እኔ እወስዳለሁ አንተ ብቻ እንዳመጣው ፍቀድልኝ አለችውና ከብዙ አሳማኝ ምክንያት በኋላ ህፃኑ ወደነ መስከረም ቤት እንዲመጣ ተወሰነ፡፡

በመቀጠልም ሴቶችና ሕፃናት መምሪያ በመሔድ ህፃኑን ለመረከብ የሚሞሉ ፎርሞችን በመፈራረም ህጋዊ አድርጌ ህፃኑን እንደ ልጄ ላሳድግ ወደ ቤት ወሰድኩት ትላለች፡፡ ሆኖም ግን ህፃኑን በምረከብበት ወቅት ተጎሳቁሎ ነበር ያገኘሁት፡፡ ሙሉ ምርመራ ተደርጎለት ሙሉ ጤነኛ ቢሆንም 4ዐ ቀናት ሆስፒታል በቆየበት ወቅት ተገቢው ጥንቃቄ ስላልተደረገለት ተጎድቶ ነበር፡፡

አሁን ህፃኑ 11 ወራትን አስቆጥሯል፡፡ እስከ 6 ወራት ከራሷ ልጅ ጋር እንደ መንታ ሳትለያቸው ጡቷን አጥብታ አሳድጋለች፡፡ አምጣ ከወለደቻት ልጅዋ በላይ ትንሰፈሰፍለታለች እሱ ከፈጣሪ የተሰጠኝ የአደራ ልጄ ነው ትላለች፡፡

አሁን የገጠማት ችግር ሕፃኑ ሆስፒታል በነበረበት ወቅት ባለቀሰ ቁጥር ጡጦ ብቻ ይሰጠው ስለነበር ከልክ በላይ ይጠባል እንጂ ሌሎች እንክብካቤ ስላልተደረገለት የሆድ መለጠጥ አጋጥሞታል፡፡ የተለያዩ ምግቦችን አሰናድቼ ብመግበውም ከዚህ ቀደም የደረሰበት ጉዳት ስለነበረበት የተመገበው ምግብ በሰውነቱ ከመዋሃድ ይልቅ ስለሚወጣ ሕፃኑ ሰውነቱ ተጎድቷል፡፡

ህፃኑ ከመጀመሪያው ጉዳት ስለገጠመው እንደ ልጅ አይጫወትም፣ ያለቅሳል፣ ይነጫነጫል፤ በተደጋጋሚ ሐኪም ቤት ብትወስደውም በሂደት እንደሚስተካከል ነው የነገሩኝ፡፡

እኛም በቦታው ተገኝተን ሕፃኑን ባየንበት ወቅት የጤንነት መጓደል እና ከአሳዳጊው እናት በስተቀር ሌላ ሰው እንዲይዘው ባለመፈለጉ ምክንያት ስራዋን በአግባቡ መስራት እንዲሁም ለወለደቻት ሕፃን ተገቢውን ጊዜ አለመስጠትና ሌሎችም ተደራራቢ ችግሮች እንደገጠሟት ተገንዝበናል፡፡

ዘጋቢ፡ ሐና በቀለ