ሀዋሳ፡ የካቲት 07/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ “በባህል እሴቶች፣ ሀገር በቀል ዕውቀት ብዘሃ ባህል አብሮነት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አሉታዊ መጤ ባህሎች” ዙሪያ ለዞን ባህል ቱሪዝምና ሰፖርት መምሪያ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ በኮንታ ዞን እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና ባህል ቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ አክሊሉ ለማ በመክፈቻ ንግግራቸው ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የባህል ተምሳሌት እና አገር በቀል ዕውቀት ከፍ ለማድረግ እንደዚህም ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶችንና መጤ ጎጂ ባህሎችን ለማስቀረት ባለድርሻ አካላትን ለማነቃቃትና በቅርበት ለመስራት ትኩረት የተደረገበት ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ፋሲካ ሙሉጌታ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የመኸር እርሻ የማሳ ዝግጅት ቢያደርጉም በቂ ግብዓት አለማግኘታቸውን ገለጹ
ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የህዝብና የመንግስት አገልግሎቶችን የሚያፋጥን በመሆኑ ለሁሉም ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ