ኮሚሽኑ በክልል፣ በፌዴራል እና በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ ነው – የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፍን አርአያ
ሀዋሳ፡ የካቲት 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኮሚሽኑ በክልል፣ በፌዴራል እና በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፈሰር መስፍን አርአያ አስታወቁ።
ኮሚሽኑ በአገሪቱ በሚገኙ 1400 ወረዳዎች ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የኮሚሽኑን ተደራሽነት ለማጠናከር እስከአሁን የተከናወኑ ተግበራትን አስመልክተው ዋና ኮሚሽነሩ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በትግራይ ክልል ካሉት ወረዳዎች፣ ከጥቂት ኦሮሚያ ክልል ወረዳዎችና ከአማራ ክልል ውጪ ባሉት በሁሉም ክልሎች የተሳታፊዎች ልየታና መረጠ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱንም ኮሚሽነር መስፍን አብራርተዋል።
የተሳታፊዎች ልየታና መረጣ በተካሄደባቸው ክልሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ ለመጀመር ኮሚሽኑ ላይ በዝግጅት እንደሆነም ተናግረዋል።
አጀንዳ የማሰባሰቡ ሥራ በፌዴራል ደረጀ እና በተለያዩ የውጭ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጭምር እንደሚሠራም የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አስታውቀዋል።
አገራዊ ምክክሩ አሳታፊ መሆን ስላለበት የታጠቁ፣ ያኮረፉ እንዲሁም የተቃየሙና በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ አካለት ጭምር መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።
ለኮሚሽኑ ሀሳብና አስተያየት በቀላሉ መስጠት የሚቻልበትን 8112 የተሰኘ የነጻ የስልክ ጥሪና የአጫጭር ጽሁፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከልም ይፋ ሆኗል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ