ሀዋሳ፡ የካቲት 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኮሬ ዞን ማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ የተቋማትን የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል፡፡
የኮሬ ዞን ማህበራዊ ክላስተር፣ የትምህርት መምሪያ፣ የዞኑ ጤና ዩኒት፣ የወጣቶችና ስፖርት፣ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀይል ልማት ዩኒት ፣ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ፣ የቴክኒክና ሙያ እና የሌሎች ተዛማጅ ተቋማትን የስድስት ወራት አፈጻጸም ገምግሟል።
በግምገማው በትምህርት ዘርፍ፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና ከትምህርት ተደራሽነት ፣ ከትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍና ሌሎች ተግባራት አንጻር በጥንካሬ ተነስቷል፡፡
ከጎልማሳ ትምህርት እና ከመጻሕፍት ተማሪ ጥምርታ አንጻር ግን ትኩረት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
የተማሪዎች ክልላዊ እና ሀገራዊ ምዘናዎች ውጤት ከፍተኛ ችግር ያለበት በመሆኑ በቀጣይ ውጤትን ከ50 በመቶ በላይ ለማድረግ መሥራት እንደሚያስፈልግ እና የትምህርት ችግርን ለመፍታት በጥናት መደገፍ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡
በገጠሩ አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች በትምህርት ቤቶች በመገኘት ከመምህራን እና ከሌሎች የትምህርት ባለድርሻዎች ጋር በትኩረት መሥራት እንዳለባቸው መክሯል።
በጤና በኩል የክትባት አገልግሎትን ጨምሮ የተሰሩ ጠንካራ ተግባራትን ማስቀጠል እንደሚያስፈልግና ከጨቅላ ህጻናት እና እናቶች ሞት መከላከል፣ ከመድሃኒት አቅርቦት፣ ከሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከጤና ኬላዎች እና ጤና ኤክስቴንሽን አገልግሎት አንጻር ያሉ ክፍተቶች ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።
በወጣቶችና ስፖርት ዩኒት ከተፈጸሙ ተግባራት ከወጣቶች ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ከስፖርታዊ ውድድሮች አንጻር የማህበራዊ ክላስተር ዘርፉ በጥንካረ የገመገመ ሲሆን፣ በዩኒቱ ምቹ የሥራ ቦታ ያለመኖር እና በወጣቶች የመዝናኛ ማዕከላት የሚታዩ ችግሮች እንደክፍተት ተወስዷል።
ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ አንጻር የሠራተኞች ደህንነት ትኩረት ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን አረጋዊያን በቋሚነት የሚደገፉበትን መንገድ አቅዶ መሥራት እንደሚያስፈልግ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ከቴክኒክ እና ሙያ አንጻር በኮሌጁ ያለው የግብዓት ችግር፣ ከCOC አሰጣጥ፣ ከኮሌጁ የመንገድ መሻገሪያ ድልድይ እና ሌሎች ውስጣዊ ችግሮችን በመለየት መሥራት እንደሚያስፈልግና እና በግል ኮሌጆች በኩልም ከደረጃ አንጻር ክፍተቶች ያሉ በመሆናቸው እንደ ማህበራዊ ዘርፍ በጋራ መፍታት እንደሚጠይቅ ተመላክቷል።
የኮሬ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እና የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ታደለ አሸናፊ እንደገለጹት በቀጣይ ተግባራትን በዕቅድ መምራትና በግብረ መልስም ማጀብ ያስፈልጋል።
የተፈጸሙ ተግባራትን ወስደን ፣ ባልተፈጸሙት ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት አለብን ያሉት አቶ ታደለ ከሠራተኞች አንጻር፣ የሠራውን መሸለም እና ባጠፋው ላይ ተጠያቂነትንም መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ እስራኤል ቅጣው – ከይ/ጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ