ፀሐይ አውሮፕላን ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት
ሀዋሳ፡ የካቲት 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ በደመቀ ሁኔታ አቀባበል ተደርጎላታል።
እ.አ.አ በ1935 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ ተገጣጥማ በረራ ያደረገችው ፀሐይ አውሮፕላን ከበርካታ ዓመታት በኋላ ዛሬ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትደርስ በደመቀ ሁኔታ አቀባበል እንደተደረገላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል።
በጀርመናዊው ኢንጅነር ሄር ሉድዊግ ዌበር እና የኢትዮጵያ ባለሞያዎች ትብብር የተሰራችው “ፀሐይ” አውሮፕላን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዲፕሎማሲ ጥረት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ መብቃቷ ይታወቃል።

More Stories
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ