የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የጠቅላይ፣ ከፍተኛና ወረዳ ፍርድ ቤቶች ዳኞችን ሹመት አፀደቀ
የክልሉ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገብረ ማርያም በምልመላውና መረጣው ያለፉ ዳኞችን ለጉባኤው አቅርበዋል።
ነፃና ገለልተኛ ዳኝነትን ለማሳደግ የወጡ የምልመላ መስፈርቶችን ያሟሉትን የፅሁፍ ፈተናም በመፈተን፤ የዳኝነት ስነምግባርንም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ ማጣሪያዎችን በዳኞች ጉባኤም በማካሄድ ለሹመት መቅረባቸውን አብራርተዋል።
የተሾሙ ዳኞችም ለክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች፣ ለወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች መሆናቸውም ተገልጿል።
በቀረቡ ዕጩዎች ዙሪያ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶ የ66 ዳኞች ሹመት በአባላቱ ሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
በምክር ቤቱ የተሾሙ ዳኞችም ቃለመሃላ ፈፅመዋል።
ከትላንት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የክልሉ ምክር ቤት ጉባዔም ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ