የአሪ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2016 የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም የውይይት መድረክ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተካሄደ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአሪ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አንተነህ በላይ፤ ህዝቡ በተቋሙ በሚረካ መልኩ የዳኝነት ሥራው እንዲከናወን እየተሠራ መሆኑን ገልፀው በግማሽ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ተሳታፊዎች በጥልቀት በመገምገም ችግሮች እንዲለዩና ጥንካሬዎች ጎልብተው እንዲቀጥሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እየቀረበ ሲሆን ተሳታፊዎች ገንቢ አስተያየቶችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ደቡብ ሱዳንን አስጠነቀቀ
የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 32ኛ የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር ፎረም እያካሄደ ነው
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችን የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ