ምክር ቤቱ የፍትሕ ሚኒስቴርን የ6 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እያዳመጠ ነው
ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ባለፉት 6 ወራት ለ 6ሺ 13 ዜጎች ነጻ የሕግ አገልግሎት የተሰጠ መሆኑን በሪፖርታቸው አመላክተው የህም የዕቅዱ መቶ ፐርሰንት መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለ58 ሺህ 4 መቶ 78 በማረሚያ ቤትና በፖሊስ ማረፊያ ቤት በሕግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ታራሚዎችን በመጎብኘት በተገኙ ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ በሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ በተሰራው ስራ ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን፣ ከቦትስዋና እና ከቻይና መንግስት ጋር በአሳልፎ መስጠትና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለማድረግ ረቂቅ ስምምነቶች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸውና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ መደረጋቸውን ሚኒስትሩ በሪፖርታቸው ማመላከታቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያሳያል፡፡
More Stories
የካፋ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው
በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን ተከትሎ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤውን በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው