የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል

ሀዋሳ፡ ጥር 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) 6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሄዳል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው መደበኛ ስብሰባው ቀዳሚ አጀንዳ የሆነውን የ12ኛ መደበኛ ስብሰባን ቃለ ጉባዔ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

በመቀጥልም የፍትህ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዳመጥ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ይደረግበታል፡፡

ምንጭ ፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት