የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ የ2016 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የቀሪ ወራት ዕቅድ ምክክር እያካሄደ ነው

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ የ2016 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የቀሪ ወራት ዕቅድ ምክክር እያካሄደ ነው

ሀዋሳ፡ ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ቢሮ የ2016 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የቀሪ ወራት ዕቅድ ምክክር መድረክ በጂንካ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በማካሄድ ነው የጀመሩት።

በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆችና የሁሉም ዞን መምሪያ ኃላፊዎች የውጉባኤ ተሳታፊ ሲሆኑ፥ የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ እንግዶችን የብዝሃ ብሔረሰቦች መገኛ ወደሆነችው አሪ ዞን ጂንካ ከተማ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዞኑ ሦስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መካከለኛ ሙያተኞችን በማሰልጠን ላይ እንደሚገኝ ገልፀው በእነዚህም በርካታ ሰልጠኞች ታቅፈው የሙያ ሽግግር እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ፥ በክልሉ ስር የተቋቋሙ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች መካከለኛ የሰለጠኑ ዜጎችን እንዲያፈሩ ትልቅ ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው ሁለት ቀናት የ2016 ዓ/ም 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን በጥልቀት በመገምገም ጉድለቶች እንዲታረሙና ቀጣይ ሥራዎች በተሻለ መልኩ እንዲሳለጥ በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን