በስፖርቱ ዘርፍ የጀመራቸውን ሥራዎች በማጠናከር ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት አንደሚሠራ ዩኒቨርሲቲው ገለፀ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በስፖርቱ ዘርፍ የጀመራቸውን ሥራዎች በማጠናከር ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት አንደሚሠራ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ የአከባቢው ማህበረሰብ በዘመናዊ ታግዞ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የድርሻቸውን እየተወጣ ይገኛል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ግቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ራሳቸውን መጠበቅ መቻላቸውን የአካል ብቃት ሠሪዎች ገልፀዋል፡፡
በስፖርቱ ዘርፍ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዩኒቨርሲቲው የሚያደርገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በጂንካ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ክፍል መምህራን ተናግረዋል፡፡
በጂንካ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ አሚን ዓሊ እንደገለፀት፤ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከ 17 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ዘመናዊ የጂሚናስትክ መሣሪያዎች ተገዝተው አገልግሎት እየሰጡ እንዳለም አስረድተዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በማዳበር ጤናውን እንዲጠብቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚባክነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን ጥምር ደን መጠበቅ፣ ማስፋትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማዘመን የዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ